የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ቮልከር ተርክ፤ከጥቅምት 2023 ጀምሮ ከ ከ3መቶ በላይ የተባበሩት መንግስታት ሰራተኞች በእስራኤል ወታደራዊ ዘመቻዎች በጋዛ መገደላቸውን አስታውቀዋል።
ተርክ በመግለጫቸው ‹‹በጋዛ የሚገኘው የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እንደገለጸው ከጥቅምት 7 ጀምሮ ከ 2መቶ ሺህ በላይ ፍልስጤማውያን ተገድለዋል ወይም ቆስለዋል ይህም ከአጠቃላይ ህዝብ ውስጥ አስር በመቶውን ይይዛል›› ብለዋል፡፡
ከ3መቶ በላይ የሚሆኑ የራሳችን ባልደረቦች በእስራኤል ወታደራዊ እርምጃ መገደላቸውን መቼም አንረሳውም ሲሉ ገልጸዋል፡፡
አክለውም ከግንቦት ወር መጨረሻ ጀምሮ ምግብ ለማግኘት ሲሞክሩ ከ1 ሺህ በላይ ሰዎች መገደላቸውንም ተናግረዋል፡፡
ድርጅቱ የሰብዓዊ መብቶችን በማክበር እና ፍትሃዊ ሰላምን በማረጋገጥ የራሳቸውን መንግስት ለመገንባት ለሚደረገው ጥረት ለፍልስጤም ህዝብ አስፈላጊውን ድጋፍ ለመስጠት ዝግጁ መሆኑንም አጽንኦት ሰጥተዋል።
ሀሚድ አብደላ
ሐምሌ 22/2017 ዓ.ም
