የአይቮሪ ኮስት ፕሬዝዳንት አላሳን ኦታራ በጥቅምት ወር በሚካሄደው ምርጫ ለአራተኛ ጊዜ እንደሚወዳደሩ አስታውቀዋል።
የ83 አመቱ አዛውንት በሰጡት መግለጫ የጤንነታቸው ጉዳይአሳሳቢ አለመሆኑን አንስተው ፡፡ በቀጣዩ የስልጣን ዘመናቸው በዋናነት “የፀጥታ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ውስጥ ብሄራዊ መረጋጋትን የማስጠበቅ ፍላጎት አለኝ ” ብለዋል ።
በርካታ ተፎካካሪዎች ከዘንድሮ ምርጫ የተከለከሉ በመሆናቸው አዛውንቱ ፕሬዝደንት የምርጫው ግንባር ቀደም ተወዳዳሪ ይሆናል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
ይሆን እንጂ በርካታ የሀገሪቱ ዜጎች በፖለቲካው ምህዳር መጥበብ ተስፋ መቁረጣቸው ተዘግቧል፡፡
አይቮሪ ኮስት ከ2010እስከ 2011 በነበረው ግጭት ከሶስት ሺህ በላይ ዜጎችን አታለች፡፡
በ2020 ደግሞ ኦታራ ለሶስተኛ ጊዜ ምርጫውን አሸንፊለሁ ማለታቸውን ተከትሉ ከፍተኛ ቀውስ እና ግጭት ተከስቷል፡፡ቁጥራቸው ቀላል ያልሆኑ የተቃዋሚ እጩዎች ራሳቸውን አግለለዋል፡፡
ከ 8.7 ሚሊዮን በላይ አይቮሪኮች ድምጽ ለመስጠት መመዝገባቸው ቢቢሲ አፍሪቃ ዘግቧል፡፡
የካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤን ጨምሮ የሲቪል ማኅበራት እና የሃይማኖት መሪዎች በሀገሪቱ እያደገ የመጣውን የፖለቲካ ትኩሳት እያደገ መምጣት ስጋት አድሮባቸዋል ተብሏል።
ሐምሌ 23/2017 ዓ.ም
