ኢትዮጲያ ከአምራች ኢንዱትሪው ዘርፍ 318 ሚሊዮን ዶላር አገኘች

የኢንድስትሪ ሚኒስተር በ2017 በጀት ዓመት ከአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ 318 ሚሊዮን ዶላር ከኤክስፖርት ገቢ መግኘቱን አስታወቀ

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የወጭ ምርቶች ተወዳዳሪነት መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ዘሪሁን አበበ እንዳስታወቁት በ2017 በጀት ዓመት በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ 318 ሚሊዮን ዶላር በኤክስፖርት ገቢ መገኘቱን ገልፀዋል፡፡

አሁን ላይ በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ በየወሩ እስከ 28 ሚሊዮን ዶላር እንሚገኝ ያነሱት አቶ ዘሪሁን ከገበያ መዳረሻ አኳያም አፍሪካ ከዩናይትድ ስቴትስና ከአፍሪካ ቀጥላ ሶስተኛ ደረጃ መያዟን ተናግረዋል፡፡

ስራ አስፈፃሚው በተጨማሪም የአምራች ኢንዱስትሪዎችን የኤክስፖርት አቅም ከፍ ለማድረግ ምርትና ምርታማነትን ከማሳደግ አንፃር የአቅም ግንባታ ስራዎችን መስራት፣ የግብዓት እጥረት ችግርን ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መፍታት፣ ከጉምሩክ ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩ ክፍተቶችን መቅረፍ፣በ2018 በጀት ዓመት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ትኩረት የሚሰጣቸው ተግባራት እንደሆኑ አብራርተዋል፡፡

አቶ ዘሪሁን አበበ ይህን ያስታወቁት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ለውይይት መነሻ የሚሆን የኤክስፖርት አፈፃፀም ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት ነው፡፡

አቤል እስጢፋኖስ

ሐምሌ 23/2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *