የቁጠባ ባህል እና ለሽርክና ስራ ማህበራት ያለው አመለካከት ዝቅተኛ መሆን ፈተና ሆኖበት እንደነበር ሆፕ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የህብረት ስራ ማህበር አስታወቀ።
ማህበሩ በ2017 በጀት ዓመት ከ80 ሚሊየን ብር በላይ የብድር አገልግሎት መስጠቱን አስታውቋል።
ማህበሩ በቆይታው ከ1መቶ 28 ሚሊየን ብር በላይ ብድር ማመቻቸቱንም ገልጿል።
በዚህ የብድር አገልግሎት ከ3መቶ በላይ ለሚሆኑ ግለሰቦች እና ማህበራት የስራ ዕድል መፈጠሩ ተነግሯል።
በቀጣይ አመት ከ5 ሺህ በላይ ሰዎችን ለመመዝገብ እቅድ መያዙንም ማህበሩ አስታውቋል።
ማህበሩ ይህን ያለው 2ኛ ዓመት 4ኛ መደበኛ የምክር ቤት ጉባኤ ባደረገበት ወቅት ነው።
ሀሚድ አብደላ
ሐምሌ 28/2017 ዓ.ም
