በ2017 ዓ/ም በፌደራል ፍርድ ቤቶች 190,347 መዛግብት ዕልባት መስጠት መቻሉን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሰጠው መግለጫ ይፋ አድርጓል።
” ባለጉዳዮች እንዲቀርቡና ውሣኔያቸውን እንዲሰሙ በስልክ ወይም አጭር የጽሁፍ መልእክት እስከ መስከረም 8 ቀን 2018 ዓ/ም ድረስ ባሉት ቀናት እንዲያውቁ ይደረጋል ” ብሏል፡፡
የፌደራል ፍርድ ቤቶች ዳኞች የሚሰጡት የዳኝነት አገልግሎት ክብደትና ዉስብስብነትን ግምት ውስጥ በማስገባት በቂ እረፍት እንደሚያስፈልጋቸው ታምኖበት በየዓመቱ መጨረሻ ለተከታታይ ለሁለት ወራት ማለትም ከነሐሴ 01 እስከ መስከረም 30 በከፊል ዝግ እንደሚሆኑ ይታወቃል።
በዚህም መሰረት ከዛሬ ከነሐሴ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በከፊል ዝግ ይሆናሉ፡፡
ፍርድ ቤቶቹ በከፊል ዝግ ሆነው በሚቆዩበት የሁለት ወራት ጊዜ በባህሪያቸዉ አስቸኳይ የሆኑና ጊዜ የማይሰጡ እንዲሁም ለዉሳኔ የደረሱ መዛግብትን መርምሮ ውሣኔ የመስጠት አገልግሎቶች እንደሚቀጥሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አሳውቋል።
ነሐሴ 1/2017 ዓ.ም
