በክልሉ ያለውን የወባ ስርጭት ለመከላከል የተለያዩ ስራዎች ቢሰሩም በሚፈለገው ልክ መቀነስ አለመቻሉን የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ አስታውቋል፡፡
የቢሮው የበሽታዎች መቆጣጠር እና መከላከል ቡድን መሪ የሆኑት አቶ አረጋይ ገብረ መድህን ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት የአጎበር አቅርቦቱ እና አጠቃቀሙ ዝቅተኛ መሆን ላለመቀነሱ ዋነኛ ምክንያቶች ናቸው ፡፡
እንዲሁም ቢሮው ተደራሽ ከሚሆንባቸው 84 ወረዳዎች፤ በዚህ ዓመት የኬሚካል እርጭት የነበረው በ 4 ወረዳዎች ላይ ብቻ በመሆኑ ስርጭቱን መቀነስ አልቻልንም ብለዋል፡፡
በተጠናቀቀው 2017 በጀት አመትም 3 መቶ 21 ሺ ሰዎች በወባ በሽታ ተይዘው እንደነበር እና 17 የሚሆኑት ለሞት መዳረጋቸውን ተናግረዋል፡፡
የወባ በሽታ ስርጭትን ለመቀነስ መንግስት እና አጋር ድርጅቶች ትብብራቸውን በማጠናከር አብረውን ሊሰሩ ይገባል ሲሉም ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡
ሐመረ ፍሬው
ነሐሴ 5/2017 ዓ.ም
