የኢትዮጵያ ኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ከ5.9 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ማገኘቱን አስታወቀ

ኮርፖሬሽኑ በ2017 የበጀት ዓመት ያገኘው ገቢ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ7 በመቶ ጭማሪ አንዳለው አስታውቋል።

ግብርና ፤ ጤና አጠባበቅ፤ ግንባታ እና ማኑፋክቸሪንግን ጨምሮ ለተለያዩ ወሳኝ ዘርፎች አስፈላጊ የሆኑ ኬሚካሎችን ከማቅረብ በተጨማሪ የውጭ ምንዛሪን በመቀነስ ቁልፍ የልማት አጋር በመሆን እየሠራ መሆኑን ገልጿል ።

በሀገር ውስጥ ከሚያመርታቸው ኬሚካሎች መካከልም፦ ሰልፈሪክ አሲድ፣ ሃይድሮጂን ፔርኦክሳይድ እና ቀደም ሲል ከውጭ ሀገር ይገባ የነበረው አሉሚኒየም ሰልፌት ይገኝበታል።

የአግሮ ኬሚካሎችን በተመለከተ የፀረ-አረም፣ የፀረ-ተባይ እና የስንዴ ዋግ መከላከያን ጨምሮ 22 አይነት ኬሚካሎችን አምርቷል፡፡

ምርቶቹም የዓለም አቀፉን የምግብ እና እርሻ ድርጅት እንዲሁም የዓለም ጤና ድርጅት የጥራት ደረጃዎችን ያሟሉ ናቸው መባሉን ተዘግቧል።

ነሐሴ 5/2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *