የአውሮፓ ህብረት መሪዎች ዩክሬን ከትራምፕ-ፑቲን ጉባኤ በፊት የወደፊቱን የመወሰን ነፃነት ሊኖራት ይገባል አሉ

ትርጉም ያለው ድርድር ሊደረግ የሚችለው የተኩስ አቁም ወይም የጠላትነት ቅነሳ በሚኖርበት ሁኔታ ብቻ ነው” ያሉት መሪዎቹ “የዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ የዩክሬን እና የአውሮፓን ወሳኝ የደህንነት ጥቅሞች መጠበቅ አለበት የሚል እምነት አለን” ብለዋል።

ሰኞ ምሽት ላይ የተስማሙበት እና ማክሰኞ የታተመው መግለጫ ሃንጋሪን ሳይጨምር በሁሉም የአውሮፓ ህብረት አባል አገራት መሪዎች ተቀባይነት አግኝቷል።

አውሮፓውያን እና ዩክሬን ከ1945 ጀምሮ በአውሮፓ ትልቁን የመሬት ጦርነት ያካሄዱት ፑቲን ተስማሚ ቅናሾችን ሊያገኙ እና የሰላም ስምምነትን ያለነሱ ሊያዘጋጁ ይችላሉ የሚል ስጋት አላቸው።

መሪዎቹ “ፕሬዚዳንት ትራምፕ ሩሲያ በዩክሬን ላይ የከፈተችውን ጦርነት ለማቆም ያደረጉትን ጥረት እንደምንቀበል እንገልጻለን” ብለዋል። ነገር ግን “በዩክሬን ውስጥ ለሰላም የሚወስደው መንገድ ያለ ዩክሬን ሊወሰን አይችልም” ሲሉ አስምረውበታል።

“ፍትሃዊ እና ዘላቂ ሰላም መረጋጋትን እና ደህንነትን የሚያመጣው አለም አቀፍ ህግን ማክበር አለበት። ይህም የነጻነት፣ ሉዓላዊነት፣ የግዛት አንድነት መርሆዎችን እና አለም አቀፍ ድንበሮች በሃይል መቀየር እንደሌለባቸው ያካትታል” ብለዋል።

የአውሮፓ መሪዎች ረቡዕ የጀርመን ቻንስለር ፍሬድሪክ ሜርዝ በጠሩት ስብሰባ ላይ ትራምፕን ለዩክሬን ጉዳይ ለመሳብ አዲስ ሙከራ ያደርጋሉ። ትራምፕ እንደሚሳተፉ አላረጋገጡም ፣ ነገር ግን “ፑቲንን ከመገናኘቴ በፊት የሁሉንም ሰው ሀሳብ እሰበስባለሁ” ብለዋል ሲል ዘ-ጋርድያን አስነብቧል።

ሀኒፍ ሀምዛ

ነሐሴ 6/2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *