በአፍጋኒስታን በደረሰ የአውቶቡስ አደጋ ህጻናትን ጨምሮ 76 ሰዎች ሞቱ

ከኢራን የተባረሩ በደርዘን የሚቆጠሩ አፍጋኒስታውያን በአውቶቡስ አደጋ ሕይወታቸው አለፈ።

በምዕራብ አፍጋኒስታን ከኢራን የተመለሱ ስደተኞችን የጫነ አውቶቡስ ከጭነት መኪና እና ሞተር ሳይክል ጋር በመጋጨቱ ቢያንስ በርካታ ህጻናትን ጨምሮ 76 ሰዎች መሞታቸው ተዘግቧል።

ግጭቱ ከተፈጠረ በኋላ አውቶቡሱ ላይ እሳት ተነስቷል ነዉ የተባለዉ።

ፖሊስ የአደጋው መንስኤ የአውቶቡሱ ሹፌር ‹‹ከመጠን ያለፈ ፍጥነት እና ቸልተኝነት››ነው ብሏል።

ቀደም ሲል ኢራን ህጋዊ ያልሆኑ አፍጋኒስታውያን በፈቃደኝነት እንዲወጡ በሐምሌ ወር ቀነ ገደብ ሰጥታ የነበር ቢሆንም፤ከእስራኤል ጋር ለአጭር ቀናት የቆየ ጦርነት ካደረገች በኋላ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ አፍጋኒስታውያንን በኃይል መልሳለች፡፡

ኢራን የብሄራዊ ደህንነት ስጋት አለብን በማለት ምክንያት ብታቀርብም፤ ተቺዎች ግን ቴህራን በእስራኤል ጥቃት ያጋጠሟትን የደህንነት ጉድለቶች ለማጣጣል ሰበብ እየፈለገች ነው ይላሉ።

በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኤጀንሲ መረጃ መሰረት፤ ከጥር ወር ጀምሮ ከ 1.5 ሚሊየን በላይ አፍጋኒስታውያን ኢራንን ለቀዉ ወጥተዋል።

አፍጋኒስታን የታሊባን መንግስት በስልጣን ላይ ባለበት ሀገር በኃይል የሚመለሱ ዜጎችን ለመቀበል አቅም እንደሌላት ብዙዎች ያስጠነቅቃሉ ሲል ቢቢሲ በዘገባው አስነብቧል።

ሀኒፍ ሀምዛ

ነሐሴ 14 /2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *