“ለበረራ አመቺ ባልሆነ ጭጋጋማ የአየር ፀባይ ምክንያት በተወሰኑ ጣቢያዎች የሚደረጉ በረራዎች ለጊዜው ቆመዋል” የኢትዮጵያ አየር መንገድ

የአየሩ ሁኔታ ሲሻሻል መደበኛ በረራዎች ወዲያውኑ የሚቀጥሉ መሆኑንም አየር መነገዱ አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዛሬ ባወጣው መግለጫ በሀገራችን ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ባለው ለበረራ አመቺ ያልሆነ ጭጋጋማ የአየር ፀባይ ምክንያት በርከት ያሉ የሀገር ውስጥ በረራዎቻችን ነሐሴ 13 ቀን 2017 ዓ.ም መስተጓጎል ገጥሟቸዋል ብሏል።

በዛሬው ዕለትም ተመሳሳይ የአየር ፀባይ በተወሰኑ ጣቢያዎች ላይ ሰለተስተዋለ ወደ እነዚህ ጣቢያዎች የሚደረጉ በረራዎች ማድረግ አልተቻለም ሲል ገልጧል።

በመሆኑም የአየሩ ሁኔታ ሲሻሻል መደበኛ በረራዎች ወዲያውኑ የሚቀጥሉ መሆኑን የገለጸው አየር መነገዱ በዚህ ምክንያት ለተፈጠረው የደንበኞች መጉላላትም ይቅርታ ጠይቋል፡፡

ነሐሴ 14 /2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *