ኢሰመኮ ጥናት አደረግኩባቸው ባለው አብዛኞቹ ማሳደጊያ ተቋማት፤ የአካል ጉዳት ሁኔታን የቅበላ መሥፈርት በማድረጋቸው አካል ጉዳተኛ ሕፃናትን ተቀብለው የማያሳድጉ መሆናቸዉን አረጋግጫለሁ ብሏል።
ይህን ያለው ተቋሙ ባወጣዉ ሪፖርት ነው።
በማሳደጊያ ተቋማቱ ለሕፃናት የሚቀርበው ምግብም በተገቢ ሁኔታ በጥራት እንደማይዘጋጅ በሪፖርቱ ተጠቅሷል።
በክልል በሚገኝ አንድ የሕፃናት ማቆያ ዉስጥ በምግብ ዕጥረት ምክንያት ህይወታቸዉ ያለፉ ሕፃናት መኖራቸዉንም ነው ኢሰመኮ በሪፖርቱ ያስታወቀው።
በህፃናት ማቆያ እና ማገገሚያ ማዕከል ከ6 ወር በታች ዕድሜ ያላቸዉ 6 ህፃናት በምግብ ዕጥረት ምክንያትና በባክቴሪያ ህመም መሞታቸዉን ሪፖርቱ ጠቁሟል።
በሌላ በኩል ኮምሽኑ በአዲስ አበባ ክትትል ከተደረገባቸው ተቋማት መካከል፤ የአንድ የህፃናት ማቆያ ከፍተኛ የሕክምና ክትትል እና ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ሕፃናት በመንግሥት መድኃኒት የማይቀርብላቸው በመሆኑ በውድ ዋጋ በመግዛት እንዲያቀርብ መገደዱን አንስቷል።
በአዲስ አበባ እና በክልል በሚገኙየሕፃናት ማሳደጊያዎች የተሰባጠረ መረጃ አያያዝ ሥርዓት አለመኖሩንም በሪፖርቱ ገልጿል።
በሕፃናት አስተዳደግና እንክብካቤ ዙሪያ ተያያዥ እና ተከታታይ ስልጠናዎች በበቂ ሁኔታ አለመሰጠታቸው እንደ ምክንያት የሚነሱ መሆናቸውን ኮምሽኑ አስታውቋል።
ሊዲያ ደሳለኝ
ነሐሴ 19/2017 ዓ.ም
