ፈረንሳይ ከ20 ዓመታት ጥበቃ የሳካላቫ የራስ ቅሎች ለማዳጋስካር መለሰች

ፈረንሳይ ከ20 ዓመታት ጥበቃ በኋላ ለ128 ዓመታት በፓሪስ ሙዚዬም የቆዩትን ሶስት የሳካላቫ የራስ ቅሎች ለማዳጋስካር መለሰች

ከራስ ቅሎቹ መካከል እ.ኤ.አ በ1897 በቅኝ ገዢ ወታደሮች አንገቱ የተቆረጠው የሰማዓቱ ንጉስ ቶኤራ ይገኝበታል።

የንጉሱ የራስ ቅል በመቶዎች የሚቆጠሩ የማላጋሲ ተወላጆች በተገደሉበት በአምቢኪ የቅኝ ግዛት እልቂት ሥፍራ ላይ ይቀበራል።

አውስትራሊያ፣ አርጀንቲና እና አልጄሪያ ከፈረንሳይ የሰው ቅሪቶች እንዲመለስላቸው እየጠየቁ ነው። ፈረንሳይ እ.ኤ.አ በ2023 ያወጣችው ሕግ ቅርሶችን መመለስ የሚያስችል ቢሆንም የመመለስ ሂደቱ አሁንም ረጅም ጊዜን ይወስዳል እንደ ቢቢሲ ዘገባ።

ነሐሴ 21 /2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *