ሁሉም የሀገሪቱ ባንኮች በጋራም ሆነ በተናጠል ዲጂታል የኃዋላ ማስተላለፊያ አማራጭ ሊኖራቸው ይገባል ተባለ።

ዳሽን ባንክ እና የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ በጋራ ሆነው አዲስ የሪሚታንስ ኢኮ ሲስተም (remittance Eco system)ይፋ አድርገዋል።

ይህ ቴክኖሎጂ ይፋ በሆነበት መድረክ የተገኙት የብሄራዊ ባንክ ገዢው አቶ ማሞ ምህረቱ ሁሉም የሀገሪቱ ባንኮች በጋራም ሆነ በተናጠል ዲጂታል የኃዋላ ማስተላለፊያ አማራጭ ሊኖራቸው እንደሚገባ ጠቁመዋል።

መንግስት በህገወጥ የውጭ ምንዛሬ ገበያ ላይ በሚሳተፍ አካላት ላይም የማያዳግም እርምጃ መውሰድ እንደሚቀጥል የብሄራዊ ባንክ ገዢው አቶ ማሞ ምህረቱ አስታውቀዋል።

የብሄራዊ ባንክ ዋና ገዢው አቶ ማሞ በህገወጥ መንገድ የሚደረግ የውጭ ምንዛሬ ስርዓት እርምጃው ድርድር የለውም ሲሉ ተናግረዋል።

በህገወጥ የውጪ ገንዘብ ስርዓቱ የሚሳተፍ አካላትን እየተቆጣጠርን ነው ያሉት አቶ ማሞ በአሁኑ ሰዓት የኢትዮጲያ የውጪ ምንዛሬ ገበያ
ስርዓት የተረጋጋ ምእራፍ ላይ ደርሷል ብለዋል።

ነገር ግን በሚፈለገው ልክ በቂ የውጭ ምንዛሬ በህጋዊው ስርዓት ወደ ሀገሪቱ ገቢ እየሆነ አይደለም ተብሏል።

ህጋዊው መንገድ ሊሰፋ ይገባል ያሉም ሲሆን በተለይ ውጪ ያሉ ኢትዮጲያውያንና ትውልደ ኢትዮጲያውያን ዜጎች በተለያየ ምክንያት በህጋዊ መንገድ ገንዘብ ለመላክ እየፈለጉ የዲጂታል የሪሚታንስ (የኃዋላ) ስርዓት ባለመኖሩ በሚፈለገው ልክ እየላኩ አይደለም ሲሉ አንስተዋል።

ለዚህ ቴክኖሎጂው እንዲሁም ሁሉም ባንኮች ሊሰሩ ይገባል ነው ያሉት።

የሀገሪቱ ባንኮች በዚህ ላይ በቂ ስራን እንዳልሰሩም ጠቁመዋል።

ጤናማ የውጪ ምንዛሬ ፍሰት እንዲኖር ህጋዊ መንገድን የሚከተሉ አካላትን እንደግፋለን ብለዋል።

ዋና ገዢው አቶ ማሞ ምህረቱ ይህንን ያሉት በዛሬው እለት የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ እና ዳሽን ባንክ በጋራ ሆነው ይፋ ያደረጉት ሪምታንስ ኢኮ ሲስተም ወደ ስራ መግባቱን አስመልክቶ ነው።

ይህ ከውጪ የሚላክ ገንዘብ ህጋዊነቱን ጠብቆ ወደ ሀገር እንዲገባ የሚያስችለው ሪሚታንስ ኢኮ ሲስተም ኢትዮጲያ ሪሚታንስ፣ጊፍት ሪሚታንስ፣ እና ኤጀንሲ ሪሚታንስ የተሰኙ ሲስተሞች ያሉት ሲሆን በኤግል ላይን ሲስተም ቴክኖሎጂስ በልፅገው በዛሬው እለት ይፋ ተደርገዋል።

የውልሰው ገዝሙ

ነሐሴ 21 /2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *