በዛሬው ዕለት በደረሰ የመንገድ ትራፊክ አደጋ የሦስት ሰዎች ህይወት ማለፉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ገለጸ።

ዛሬ ከጠዋቱ 12:40 ሠዓት በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 5 ልዩ ቦታው ሳንሱሲ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በደረሠ የመንገድ ላይ የትራፊክ አደጋ የ3 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ14 ሠዎች ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት ደርሷል።

የጉዞ አቅጣጫውን ከሳንሱሲ ወደ ፒያሳ ያደረገ የሠሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3 A 49812 አ/አ የሆነ ሸገር ባስ በቦታው ላይ ከሚገኝ ተርሚናል ተሳፋሪዎችን ጭኖ በሚወጣበት ወቅት በተመሳሳይ አቅጣጫ ጉዞውን ካደረገ  የሠሌዳ ቁጥር ኮድ 3 A 69183 አ/አ ከሆነ አንበሳ የከተማ አውቶቡስ ጋር ተጋጭተው በወቅቱ ትራንስፖርት በመጠበቅ ላይ የነበሩ 3 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ በ14 ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሷል።

የመንገድ ትራፊክ አደጋ በየጊዜው የሞት፣ የአካል ጉዳትና የንብረት ውድመት መንስኤ በመሆን ለከፍተኛ የምጣኔ ሀብትና ለተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች እየዳረገ በመሆኑ አሽከርካሪዎችም ሆኑ የመንገድ ተጠቃሚ እግረኞች ተገቢውን ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አሳስቦ የአደጋው ምክንያት እየጣራ መሆኑን ጨምሮ ገልጿል።

ነሐሴ 24/2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *