ዜጎች ግድቡን በተመለከተ መልካም ምኞታቸውን የሚገልጹበት አጭር የጽሁፍ መልዕክት መላኪያ ይፋ ተደረገ።

የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ  ግንባታው ተጠናቆ ለምረቃ ዝግጁ መሆኑን በማስመልከት ዜጎች መልካም ምኞታቸውን የሚገልጹበት ‘የትውልድ አሻራ’ የተሰኘ አጭር የጽሁፍ መልዕክት መላኪያ የኤስኤምኤስ ቁጥር 8120 ይፋ ተደርጓል፡፡

ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለግድቡ እውን መሆን ሲያደርጉት ስለነበረው ርብርብ፣ እንዲሁም መልካም ምኞታቸውን ከዛሬ ነሐሴ 27 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ መስከረም 30 ቀን 2018 ዓ.ም ደረስ ለ33 ቀናት  መላክ እደሚችሉ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር አረጋዊ በርሄ (ዶ/ር) ገልፀዋል።

የ8120 የአጭር መልዕክት መላኪያ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት እና ኢትዮ ቴሌኮም በጋራ በመሆን ያዘጋጁት መሆኑን ጽ/ቤቱ አስታውቋል።

ዜጎች መልዕክቱን ሲልኩ ከ5 ብር እስከ መቶ ብር ድጋፍ ያደርጋሉ ተብሏል።

አዲስአለም አበበ

ነሐሴ 27/2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *