ህንድ በአሜሪካ ሸቀጦች ላይ የጣለችዉን ታሪፍ ወደ ዜሮ ለማዉረድ ዕቅድ ማቅረቧን ትራምፕ ገለጹ

የአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት ከሩሲያ ዘይት ገዝታለች ሲሉ በከሰሷት ህንድ ላይ በቅርቡ የ50 በመቶ ታሪፍ መጣላቸዉ ይታወሳል፡፡

አገራቸዉ ከህንድ ጋር ያላት ግንኙነት ወደ አንድ ወገን ያጋደለ ነዉ ሲሉ ትችት ያቀረቡት ፕሬዝዳንቱ፤ ኒዉ ዴልሂ በአሜሪካ ሸቀጦች ላይ የጣለችዉን ታሪፍ ወደ ዜሮ ለማዉረድ ሃሳብ ማቅረቧን ገልጸዋል፡፡

ትራምፕ ህንድ ከሩሲያ የጦር መሳሪያዎች እና ዘይትን በመግዛቷ ተችተዋል፡፡

ይህም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ግንኙነት የበለጠ እንዲበላሽ አድርጓል ነዉ የተባለዉ።

ትራምፕ ፤ እኛ ከህንድ ጋር የምንሰራዉ ንግድ በጣም ትንሽ ነዉ ያሉ ሲሆን፤ እነሱ ግን ከእኛ ጋር እጅግ በጣም ብዙ ንግድ ይሰራሉ ብለዋል።

አሁን ታሪፋቸውን ወደ ዜሮ ለመቀነስ ሀሳብ አቅርበዋል ግን ጊዜው እያለቀ ነው፤ይህን ማድረግ የነበረባቸው ከብዙ ዓመታት በፊት ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ህንድ በትራምፕ ሀሳብ ዙሪያ እስካሁን አስተያየት አልሰጠችም፡፡

የትራምፕ ታሪፍ ጫና ብዙውን ጊዜ የውጭ መሪዎች እንደ ኢነርጂ እና የጦር መሳሪያዎች ማምረቻ ባሉ አካባቢዎች ብዙ የአሜሪካ ምርቶችን እንዲገዙ በሚያደርጉ ማበረታቻዎች የታጀበ ነው ሲል የዘገበዉ አልጀዚራ ነዉ።

እስከዳር ግርማ

ነሐሴ 27/2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *