ኘሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ሀገራቸዉ በጉልበተኞች በጭራሽ እንደማትሸበር ተናገሩ

ቻይና የጂኦ ፖለቲካዋን እና ወታደራዊ ሀይሏን እያሳየችበት ነዉ የተባለ የድል በአል አዳዲስ የጦር መሳሪያዎችን ይፋ እያደረገችበት ነዉ።

ቻይና በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ድል የተቀዳጀችበትን 80ኛ አመት ለማክበር ዛሬ በማዕከላዊ ቤጂንግ ታላቅ ​​ወታደራዊ ትርኢት እያካሄደች ትገኛለች ።

በቤጂንግ ቲያናንመን አደባባይ በተደረገው ወታደራዊ ትርኢት ቻይና ዶንግፌንግ-5 ሚሳኤልን በፈሳሽ የሚነዳ አህጉር አቀፍ ስትራቴጂካዊ የኒውክሌር ሚሳኤልን ይፋ አድርጋለች።

ሚሳኤሉ ከቻይና ሰሜናዊ ሴሎ ሜዳዎች እንዲወነጨፍ የተነደፈ ነዉ ተብሏል።

የሩስያው መሪ ቭላድሚር ፑቲን እና የሰሜን ኮሪያው ኪም ጆንግ ኡን ከቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ጋር በቤጂንግ ከሁለተኛው የአለም ጦርነት ማብቂያ በኋላ መስከረም 3 ቀን 80 አመታትን ባከበረው ወታደራዊ ትርኢት ላይ ይገኛሉ።

እነዚህ ሶስት መሪዎች በአደባባይ ሲገናኙ ለመጀመሪያ ጊዜ ይሆናል ሲል ቢቢሲ እየዘገበ ይገኛል።

ቻይና አሁንም ሁከትና ብጥብጥ ባለበት አለም ሰላማዊ እድገት ለማድረግ ቁርጠኝነቷን ገልጻለች።

ፕሬዝዳንት ዢ  ጂንፒንግ ዝግጅቱ ከመጀመሩ በፊት ባደረጉት ንግግር ሀገራቸው መቆም የማትችል እና በጉልበተኞች በጭራሽ አትሸበርም ብለዋል።

ሰልፉ ቻይና የተናገረችውን የታይዋን ዲሞክራሲያዊ ደሴት ለማጥቃት የሚያስችል እቅድ ፍንጭ ሰጥቷል ሲል ቢቢሲ  በቀጥታ ስርጭት እየዘገበ ይገኛል።

ከ50 ሺህ በላይ እንግዶች በአደባባዩ ላይ እንደታደሙ ገልፆል።

የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ሼባዝ ሸሪፍ ጨምሮ የኢራኑ ማሱድ ፔዜሽኪያን ተገኝተዋል።

ቁምነገር አየለ

ነሐሴ 28/2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *