ቀጣናዊ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቱ ኢትዮጵያ፣ ጅቡቲ፣ ደቡብ ሱዳን እና ኡጋንዳን የሚያገናኝ ነው፡፡
የትራንስፖርትና ሎጂቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ እና የጅቡቲ አቻቸው ሀሰን ሁመድ፤ የዲካሂል-ጋላፊን ፕሮጀክት ለማጠናቀቅ እና የደሱ ኮሪደርን ለማቋቋም እና ወደትግበራ ለመግባት የጋራ መግባባት ላይ ደርሰዋል።
የደሱ ኮሪደር የባሕር ባር ለሌላቸው ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን አማራጭ የንግድ መስመር ሆኖ ያገለግላል፡፡
የንግድ ፍሰቱን ማሳደግ፣ የሎጀሰቲክስ ወጪን መቀነስና ድንበር ተሻጋሪ ትስስርን ማስፋት የኮሪደሩ መገንባት ዋነኛ ግብ ነው፡፡
በዓመቱ አጋማሽ አራቱ ሀገራት የደሱ ኮሪደርን አስመልክቶ የመገባቢያ ስምምነት መፈራረማቸው የሚታወስ ነው፡፡
ነሐሴ 27/2017 ዓ.ም
