በግድቡ ዙሪያ የመርከብ ማረፊያዎችን ለመስራት የግሉ ዘርፉ እንዲሳተፍ እየተሰራ ነዉ ተባለ ።

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ኘሮጀክት የሎጀስቲክስ እና የትራንስፖርት ስራ ዙሪያ የድርሻዉን መወጣቱን የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስትር ገለፀ።

ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስትሩ ዶ/ር አለሙ ስሜ ለኘሮጀክቱ የሚያስፈልጉ ግብአትን ማጓጓዝ ፈታኝ ስራ እንደነበር አንስተዋል።

በመንገድ እና በአየር ንብረት ችግር አስቸጋሪ ሁኔታዎች ገጥመዉት እንደነበር የሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ሚኒስትር ተናግረዋል።

ከጅቡቲ ተነስቶ ጉባ እስኪደርስ መንገዱ ፈታኝ እንደነበር ያነሱት ዶ/ር አለሙ ስሜ በተለይም በጅቡቲ መስመር ከ 200 መቶ ኪ.ሜ በላይ መንገድ በሙቀት እና በምድረ በዳ ሹፌሮች ብቻቸዉን በመጓዝ አስቸጋሪ አመታትን ማሳለፋቸዉን ገልፀዋል።

ሚኒስትሩ እንደገለፁት ” ግብአቶቹ ጉባ እስኪደርሱ ጉዞዉ እንዲስተጓጎል ባደረጉ አካላት ስቃይ እና ፈተና ገጥሟቸዋል እንደነበር አስታዉሰዋል።

የመንግሥት ጥበቃ እንዳለ ሆኖ ከዛ ባመለጠ መልኩ በሰራተኞቹ ላይ እስከ ህይወት መጥፋት የሚያደርስ አደጋ ይደርስባቸዋል እንደነበር ገልፀዋል።

ሚኒስትሩ አሁን ላይ የግድቡን መጠናቀቅ ተከትሎ ለትራንስፖርት እንዲሁም ለሌሎች ስራዎች እንዲዉል ለማድረግ ስራዎች እንዳሉ ነግረዉናል።

በግድቡ ዙሪያ የመርከብ ማረፊያዎችን ለመስራት የግሉ ዘርፉ እንዲሳተፍ እየተሰራ ነዉ ይገኛል ተብሏል።

የዉሃ ትራንስፖርትን ለማዘመን እንዲሁም የመርከብ ማረፊያዎች እና አዳዲስ መርከቦችን እንዲሰሩ ለማድረግ ታስቧል ብለዋል።

ቱሪዝም እንዲሁም የአሳ እርባታን ጨምሮ ግድቡን የኢኮኖሚ ማእከል ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ቁምነገር አየለ

ጳጉሜ 3/2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *