ከ 4 ሺህ በላይ መደበኛ ነጋዴዎችን መለየቱን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታወቀ

ከ4 ሺህ በላይ መደበኛ ነጋዴዎችን ልየታ በማድረግ ወደ ስራ ለመግባት መዘጋጀቱት የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ገልጿል፡፡

የንግድ ቢሮዉ ኮምኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አሸናፊ ብርሃኑ፤ አዲሱ ደንብ የፀደቀ ቢሆንም ደንቡ ተግባራዊ እንዲሆን መመሪያ ተዘጋጅቶ  ወደ ስራ አለመገባቱን ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም ንግድ ቢሮ መመሪያው ከመጽደቁ በፊት የልየታ ስራን እያከናወነ እንደሚገኝ አስታዉቀዋል፡፡

በንግድ ቢሮው መደበኛ የሚባሉት ነጋዴዎች ንግድ ፍቃድ ወስደው በንግድ ምዝገባ ውስጥ ያሉ መሆናቸዉንም አቶ አሸናፊ ተናግረዋል፡፡

መደበኛ ያልሆኑ የሚባሉ ነጋዴዎች በንግድ መዝገብ ሳይመዘገቡና የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላወጡ ወይም ቋሚ የንግድ ቤት ወይም ቦታ የሌላቸው መሆናቸዉን ገልጸዋል፡፡

በአዲሱ አዋጅ መሰረት ከዚህ በፊት በኢ-መደበኛ የንግድ ሥርዓት ውስጥ ለሚንቀሳቀሱ ነጋዴዎች  በተሰጣቸው የሥራ ቦታ ላይ የተወሰነ የመስሪያ ጊዜ የተቀመጠ ሲሆን፤ ካፒታላቸው ከፍ ሲል ወደ መደበኛ የንግድ ሥርዓት  እንደሚካተቱ ያመላክታል፡፡

አቤል እስጢፋኖስ

ጳጉሜ 3/2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *