ፌደሬሽኑ አመሻሹን ባወጣው መግለጫ በ2 ጉዳዮች ላይ ለፊፋ ቅሬታውን አስገብቷል።
የግብፅ ደጋፊዎች ሌዘር ፖይንተር (ግብ ጠባቂው ላይ እና በሌሎች) ተጨዋቾችም ላይ በማብራት በፊፋ የተከለከለ ተግባር መፈፀሙን አንቀፅ ጠቅሶ ቅሬታ አስገብቷል ።
እንዲሁም የኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር በተዘመረበት ወቅት ደጋፊዎች ያልተገባ ነገር መፈፀማቸውን ጠቅሶ እርምት እንዲወስድ ሲል በዋና ስራአስፈፃሚው አቶ ባህሩ ጥላሁን ለፊፋ የተፃፈው ደብዳቤ ያመለክታል።
ጳጉሜ 3/2017 ዓ.ም
