የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ከእስራኤል ጋር ያላትን ግንኙነት ለማላላት ማሰቧ ተሰምቷል።
እስራኤል ዌስት ባንክን ወደተቆጣጠረችው አከባቢ የምትጠቀልል ከሆነ አምባሳደሯን ልታስወጣ እንደምትችልም አልጀዚራ ዘግቧል።
የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ሞሮኮ እና ባህሬንን ጨምሮ ከእስራኤል ጋር ግንኙነት ካላቸው ጥቂት የአረብ ሀገራት መሀል አንዷ ነች።
የአውሮፓ መንግስታት ለፍልስጤም መንግስት እውቅና እንዲሰጡ በተደረጉ ጥሪዎች ምክንያት እስራኤል ባለፉት ጥቂት ወራት የተወረረችውን ዌስት ባንክን ወደ ግዛቷ እንደምትቀላቅል ዝታለች።
በሌላ በኩል ሮይተርስ የዜና ወኪል፥ ስማቸው ያልተጠቀሱ ሶስት ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ አቡ ዳቢ ግንኙነቱን ሙሉ በሙሉ እንደማታቋርጥ ነገር ግን አምባሳደሯን ልትጠራ እንደምትችል ዘግቧል።
ሀና ሰይፉ
መስከረም 8/2018 ዓ.ም
