የ2024/25 69ኛው የባሎን ዶር አሸናፊ ኦስማን ዴምቤሌ ፣ ራፊንሃ፣ ላሚን ያማል፣ ቪቲንሃ ወይስ ሙሐመድ ሳላህ?

30 የመጨረሻ ዕጩዎች የቀረቡበት የ2024/25 69ኛው የባሎን ዶር አሸናፊ ዛሬ በፈረንሳይ ፓሪስ ይፋ ይደረጋል።

ፈረንሳዊው የፒኤስጂ የመስመር ተጨዋቸ ኦስማን ዴምቤሌ የአሸናፊነት ግምት ተሰጥቶታል።

ፒኤስጂ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን እንዲያነሣ ያስቻለው ዴምቤሌ፤ከክለቡ ጋር በተጨማሪም የፈረንሳይ ሊግ ዋን እና የአውሮፓ ሱፐር ካፕን ጨምሮ በአጠቃለይ አምስት ክብሮችን አሳክቷል።

37 ግቦችን ሲያስቆጥር 16 ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ አቀብሏል።

ትልቅ ግምት ካገኙት መካከል የባርሴሎናው ላሚን ያማል ሌላኛው ነው።

ባለፈው የውድድር ዓመት የላሊጋውን ዋንጫ ጨምሮ 3 ክብሮችን ያሳካው ላሚን ያማል ጠንካራ ተፎካካሪ ነው።

21 ግቦችን በማስቆጠር 26 ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶም አቀብሏል።

በባሎን ዶር ታሪክ እስከ አሁን ከ21 ዓመት በታች የሆነ ተጫዋች አሸንፎ አያውቁም፤ምን አልባት የ18 ዓመቱ ስፔናዊው ኮከብ ላሚን ያማል አዲስ ታሪክ ሊያስመዘግብ ይችላል ተብሏል።

የፒኤስጂው ቪቲንሃ እና የባርሴሎናው ራፊንሃም በምሽቱ መድረክ ከሚጠበቁ ተጨዋቾች መካከል ሆነዋል።

ከኦስማን ዴምቤሌ፣ ላሚን ያማል፣ ራፊንሃ፣ ቪቲንሃ፣ ሙሐመድ ሳላህ በተጨማሪ ኪሊያን ምባፔ፣ አችራፍ ሐኪሚ፣ ዲዚሬ ዱዌ፣ ኪቪቻ ካቫርትሽኬሊያ እና ኑኖ ሜንዴዝ የአሸናፊነት ግምት ያገኙ ሌሎች ተጫዋቾች ናቸው።

የሴቶች ባሎን ዶር በሁለቱም ፆታ የዓመቱ ምርጥ ወጣት ተጫዋች ሽልማት፤ምርጥ ግብ ጠባቂ እና ምርጥ አሠልጣኝን ጨምሮ ሌሎች ሽልማቶችም በፓሪስ ይከናወናል።

ጋዲሳ መገርሳ

መስከረም 12/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *