አዋጅ 1113/2011 ይተካል የተባለዉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ማሻሻያ ረቂቅ ለድርጅቶቹ ስራ እክል የሆኑ አሳሪ አንቀፆችን ይዟል የሚል ጥያቄ የተነሳበት ነዉ።
ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ምክር ቤት ኘሬዝደንት አቶ አህመድ ሁሴን ምክር ቤቱ አንቀፆቹ እንዲስተካከሉ ከምክረ ሀሳብ ጋር ሲያቀርብ ነበር ብለዋል።
የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን እና ፍትህ ሚኒስቴር እያዘጋጁት ያለው ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ዉስጥ ስጋት የሆኑ አንቀፆች እንዲቀሩ መደረጉንም አንስተዋል።
የአዋጁ ማሻሻያ ረቂቅ አገር በቀል የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ለ’ፖለቲካ አድቮከሲ’፣ የመራጮች ትምህርት፣ ምርጫ መታዘብ እና ማንኛውም ከምርጫ ጋር የተያያዙ ሥራዎችን ለመሥራት ከውጭ የፋይናንስ ምንጭ ገንዘብ እንዳይቀበሉ ይከለክላል አቶ አህመድን ይህንን ክልከላ እንዲወጣ ተደርጓል ብለዋል።
ሆነም አሁንም በማሻሻያ ረቂቁ ላይ የሚቀሩ ስራዎች አሉ ያሉት ኘሬዝዳንቱ ይህንምም ለባለስልጣናት መስሪያ ቤቱ ለፍትህ ሚኒስቴር ማቅረባቸውን ገልፀዋል።
በቀጣይ ረቂቁ ላይ በሚኖሩ ዉይይቶች ምክር ቤቱ መሻሻል የሚገባቸዉ አንቀፆች ላይ ከነምክረ ሀሳቦች ጋር እንዲስተካከሉ እያቀረበ ይገኛል ተብሏል።
ምክር ቤቱ እና የሲቪል ድርጅቶቹ በማሻሻያዉ ረቂቅ ላይ ቸልተኛ አልነበሩም ያሉት አቶ አህመድ በተለያዩ ዙሮች ድርጅቶቹ ዉይይቶች ሲያደርጉበት ቆይተዋል ብለዋል።
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ የ ‘አፋኝ ህጎችን ስጋት ይፈጥራል እንዲሁም የሲቪክ ምህዳሩን እንዳያጠበዉ የሚል ጥያቄ የተነሳበት መሆኑ የሚታወስ ነዉ።
ቁምነገር አየለ
መስከረም 9/2018 ዓ.ም
