ቡርኪናፋሶ፣ ማሊ እና ኒጀር ከዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (ICC) ለቀው መውጣታቸውን ገልጸዋል፡፡
ፍርድ ቤቱንም “የኒዮ-ቅኝ ገዢዎች የጭቆና መሣሪያ” በማለት ጠርተውታል።
ሦስቱ በወታደራዊ ሀይል የሚመሩ ሀገራት መቀመጫውን በሄግ ያደረገውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛ ፍርድ ቤት ስልጣንን እንደማይቀበሉ በጋራ በሰጡት መግለጫ አሳውቀዋል።
“አይሲሲ የተረጋገጡ የጦር ወንጀሎችን፣ በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን፣ የዘር ማጥፋት እና የጥቃት ወንጀሎችን ለመቆጣጠር እና ለፍርድ ለማቅረብ እንደማይችል አረጋግጧል” ብለዋል ሶስቱ መሪዎች።
ፍርድ ቤቱ በሶስቱ ሀገራት ውሳኔ ላይ እስካሁን ምላሽ አልሰጠም ፣ የሀገራቱ መሪዎች ከሩሲያ ጋር የቅርብ ግንኙነት ያላቸው መሆናቸውን ቢቢሲ አስታውሷል፡፡
የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን በICC የእስር ማዘዣ እንደወጣባቸው ይታወቃል ብሏል ዘገባው፡፡
መስከረም 13/2018 ዓ.ም
