የክለቡ ሌጀንድ ኢማኑኤል ፔቲት ሚኬል አርቴታ የአርሰናል አሰልጣኝነቱ የሚያበቃበት ቀን እንዳለው ተናግሯል።
አርቴታ በ2020 የኤፍኤ ካፕ ዋንጫን በማንሳት ለስድስት ዓመታት ያህል በአርሰናል ቆይቷል።
ከአምስት አመት በፊት የኤፍኤ ካፕ ዋንጫን ከማንሳት ውጭ ስፔናዊው ትልቅ ዋንጫ አላመጣም፤ ለሶስት ተከታታይ አመታትም የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫን ማጣቱ ይታወቃል።
ምንም እንኳን የአርሰናል እድገት ከአርቴታ የመጀመሪያ ቀን በኋላ አሁን ያለበት ሁኔታ አስደናቂ ቢሆንም፤ አሁን ግን አሰልጣኙ ቀጣዩን እርምጃ ላለመውሰድ ምንም ሰበብ የለውም የሚል ስሜት አለ።
አሁት ኢማኑኤል ፔቲት ሚኬል አርቴታ በሚቀጥለው ክረምት ከአርሰናል ሊባረር እንደሚችል አሳስቧል፡፡
የቀድሞ ፈረንሳዊው የመድፈኞቹ ኮከብ ከስታዲየም አስትሮ ጋር በነበረው ቆይታ፤ ለአርቴታ ይህ አመት እራሱን ለማሳየት የመጨረሻ አመት ነው ብሎ እንደሚያምን ገልጿል።
ኢማኑኤል”የመጨረሻ የውድድር ዘመኑ ይሆናል። አሁን ታማኝ መሆን አለብን ሚኬል አርቴታ እስካሁን እየሰራ ስለነበረው ነገር አመሰግነዋለሁ ፤እወደዋለሁ ነገር ግን ከፍተኛ ዋጋ የወጣበትን ቡድን ይዞ መፍራቱን እየቀጠለ ነው።
እኛ አርሰናል ነን ወደ ቀድሞ ክብራችን መመለስ አለብን፤እኔ ደክሞኛል ስለእናንተ አላውቅም ግን ደክሞኛል ከዚህ በላይ ትዕግስት የለኝም” ብሏል።
አርቴታ ድልን እንጂ ስኬትን አያመጣም። ይህ ማለት ዋንጫ እንደሚያሸንፉ ዋስትና አይሰጠንም።
በፕሪምየር ሊጉ ውስጥ ብዙ ገንዘብ ያላቸው እና ብዙ ገንዘብ ያወጡ ክለቦች አሉ ነገር ግን እንዳልኩት ለእኔ በዚህ የውድድር ዘመን እሱ የሚፈልገውን አግኝቷል።
በእውነት ደክሞኛል ለአርሰናል ስትጫወት ለሻምፒዮንነት መወዳደር አለብህ፤ ለኤፍኤ ካፕ ዋንጫ ትልቅ ክብር አለኝ ነገር ግን የሊጉን ዋንጫ ማንቸስተር ሲቲ እና ሊቨርፑል ሲያሸንፉ ማየት ሰልችቶኛል አሁን ተራው የኛ ነው ብሏል።
ጋዲሳ መገርሳ
መስከረም 14/2018 ዓ.ም
