የቱሪዝም ቀን በዛሬው እለት መከበር ጀመረ።

በዛሬው እለት መስከረም 15 /2018 መከበር የጀመረው የቱሪዝም ቀን ”ቱሪዝም እና ዘላቂ ለውጥ” በሚል መሪ ቃል መሆኑን የኢፌዲሪ ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከአዲስ አበባ ከተማ ቱሪዝም ኮሚሽን እና ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ጋር በመተባበር ለ 1 ወር የሚቆዩ ተንቀሳቃሽ አውደ ርዕዮችን በተለያዩ ትምህርት ቤቶች በማሳየት ለማክበር እየሰራ እንደሚገኝ ተገልጿል።

የዘንድሮ የአለም የቱሪዝም ቀን ታላቁ የህዳሴ ግድብ በተመረቀበት ማግስት መከበሩ እንደ ሀገር የምንኮራበት ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ተናግረዋል፡፡

የኢፌድሪ ቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ በበኩላቸው የሀገር ውስጥ የቱሪዝም እንቅስቃሴን ለማጠናከር እየተሰራ መሆኑን በመጥቀስ ሀገሩን የሚወድ እና የሚያዉቅ ትውልድን ለመፍጠር በማሰብ የዘንድሮን የአለም የቱሪዝም ቀን በትምህርት ቤት ውስጥ ለማድረግ ታስቦ መጀመሩን አብራርተዋል።

በዛሬው እለት የተጀመረው ተንቀሳቃሽ አውደርዕይ ለ 1ወር የሚቆይ ሲሆን በ4 የተመረጡ ትምህርት ቤቶች እንደሚካሄድ ተገልጿል።

የቱሪዝም ቀን በአለም ለ46ተኛ ጊዜ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ38ተኛ ጊዜ እየተከበረ ያለው፡፡

ሀና ሰይፉ

መስከረም 15/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *