ዶናልድ ትራምፕ ረቡዕ ዕለት በተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ንግግር ሊያደርጉ በሄዱበት ወቅት “ሶስት ጊዜ ደባ እንደተፈጸመባቸው” በመግለጽ ድርጅቱ ጉዳዩን እንዲመረምር ጠየቁ።
በማኅበራዊ ሚድያቸው መልዕክታቸውን ያሰሙት የአሜሪካው ፕሬዝደንት ከቀዳማዊ እመቤት ሜላኒያ ትራምፕ ጋር አሳንሰር (ኤስካሌተር) ሊጠቀሙ ሲሉ ማሽኑ መበላሸቱን አውስተዋል።
አክለው ንግግር ሊያደርጉ ሲዘጋጁ ፅሑፍ የሚያሳየው ማሽን (ቴሌፕሮምፕተር) እና የድምፅ መቆራረጥ እንደነበር ጠቅሰው “ሶስት ጊዜ ደባ ተፈፅሞብኛል” ብለዋል።
የተባበሩት መንግሥታት ባለሥልጣን ድምፅ ማጉያው የቀነሰው አንዳንድ ግለሰቦች በትርጉም እንዲሰሙት ለማስቻል ነው ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።
የተባበሩት መንግሥታት ቀደም ብሎ በሰጠው ምላሽ አሳንሰሩ የተባለሸው የትራምፕ ቪድዮን የሚያነሳ ግለሰብ ወደኋላ በመውጣቱ ማሽኑ ሳይቆም እንዳልቆረ ጠቁሞ ቴሌፕሮምፕተሩ ደግሞ የአሜሪካ ልዑካን ይዘው የመጡት ነው ብሏል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
መስከረም 15/2017 ዓ.ም
