6.1 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ በቬኔዝዌላ መከሰቱ ተሰምቷል

ዋና ከተማዋ ካራካስን ጨምሮ በበርካታ የቬኔዝዌላ ግዛቶች እና በጎረቤት ኮሎምቢያ ድንበር የመሬት መንቀጥቀጡ ተሰምቷል ነዉ የተባለዉ።

በቬኔዝዌላ በሚገኙ በርካታ ግዛቶች፣ እንዲሁም በጎረቤት ኮሎምቢያ ድንበር ላይ የመሬት መንቀጥቀጡ ተሰምቷል የተባለ ሲሆን፤ በአከባቢዉ የሚገኙ ነዋሪዎች የመኖሪያ እና የቢሮ ህንፃዎችን ለቀዉ ወጥተዋል፡፡

እስካሁን ምንም ጉዳት ወይም ሞት አልደረሰም።

በቬኔዝዌላ ከሀገሪቱ ህዝብ 80 በመቶው የሚሆነው በመሬት መንቀጥቀጥ ቀጠናዎች ውስጥ የሚኖር ነዉ፡፡

ከ4መቶ በላይ ሰዎችን ህይወት የነጠቀዉን እና በ2018 ከሰሜን የባህር ዳርቻ የተነሳዉ 7.2 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥን ጨምሮ፤ በአገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል ከዚህ በፊት አምስት ዋና ዋና የመሬት መንቀጥቀጦች ደርሰዋል ሲል አልዘጂራ ዘግቧል፡፡

እስከዳር ግርማ

መስከረም 15/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *