የማላዊ የቀድሞ ፕሬዝደንት የነበሩት የ85 ዓመቱ ፒተር ሙታሪካ ዳግም ምርጫ አሸነፉ

የማላዊ የቀድሞ ፕሬዝደንት የነበሩት የ85 ዓመቱ ፒተር ሙታሪካ ባለፈው ሳምንት የተካሄደውን ምርጫ ማሸነፋቸው ተነገረ።

ኦፊሴላዊ ውጤቶች እንደሚያሳዩት ሙታሪካ 57 በመቶ ድምፅ ሲያገኙ የወቅቱ ፕሬዝደንት የ70 ዓመቱ ላዛረስ ቻክዌራ 33 በመቶ ድምፅ አግኝተዋል።

ወደ ፖለቲካ ከመግባታቸው በፊት ፓስተር የነበሩት ቻክዌራ የመጨረሻው ውጤት ከመታወጁ በፊት መሸነፋቸውን አምነው ተቀብለው ለሙታሪካ ደውለው “ታሪካዊውን ምርጫ” በማሸነፋቸው የእንኳን ደስ ያለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል።

የሕግ ፕሮፌሰር የሆኑት ሙታሪካ በአውሮፓውያኑ ከ2014 እስከ 2020 የማላዊ ፕሬዝደንት ሆነው አገልግለዋል። በ2020 በቻክዌራ በሰፊ ውጤት ተሸንፈው ከመንበረ-ሥልጣን መውረዳቸው ይታወሳል።

ደቡብ አፍሪካዊቷ ሀገር የምጣኔ ሀብት ቀውስ ውስጥ የምትገኝ ሲሆን የነዳጅ እና የውጭ ምንዛሪ እጥረት ሀገሪቱን እያመሷት ይገኛሉ ሲል ቢቢሲ አፍሪካ ዘግቧል።

መስከረም 15/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *