የኢንዶኔዥያ ብሄራዊ የአደጋ አስተዳደር ኤጀንሲ 77 ተጎጂዎች ለህክምና ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውን አስታውቋል።
በምስራቅ ጃቫ ግዛት በሚገኝ አዳሪ ትምህርት ቤት ጣሪያ በመደርመሱ ቢያንስ ሦስት ተማሪዎች ሲሞቱ፤በደርዘኖች የሚቆጠሩ ደግሞ መጥፋታቸውን ባለሥልጣናት ገልጸዋል።
የብሔራዊ አደጋ አስተዳደር ኤጀንሲ እንደገለጸዉ፤ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በህንጻው ፍርስራሽ ስር ታፍነው ሊገኙ ይችላሉ ተብሎ የሚታመኑ 38 ሰዎችን እየፈለጉ ነው።
አስራ አንድ ሰዎች ከፍርስራሹ ስር መውጣታቸውን እና ሌሎች 91 ሰዎች ለማምለጥ መቻላቸውን የአደጋ አስተዳደር ኤጀንሲ አስታውቋል።
ኤጀንሲው እንዳስታወቀው 77 ተጎጂዎች ለህክምና ወደ አካባቢው ሆስፒታሎች ተወስደዋል።
ኤጀንሲው፤ አደጋው የግንባታ ደህንነት መስፈርቶችን በጥብቅ መተግበር እንደሚያስፈልግ ትኩረት የሰጠ ነዉ ብሏል፡፡
የኢንዶኔዥያ ብሔራዊ የፍለጋ እና አድን ኤጀንሲ የተባለ ተቋም ቀደም ሲል ባወጣው ሪፖርት፤ 1መቶ ተማሪዎች በአደጋው የተጎዱ ሲሆን፤ ከነዚህም ውስጥ አንዱ ብቻ በህይወት ተገኝቷል እንደ አልጀዚራ ዘገባ።
እስከዳር ግርማ
መስከረም 20/2018 ዓ.ም
