ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በምንጃር ወረዳ በአረርቲ ከተማ በደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በተከሰተውና ከ30 በላይ ለሚሆኑ ምዕመናን ህልፈት ምክንያት በሆነው አደጋ የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ገልጸዋል። By ethiofmAdminOctober 2, 2025October 2, 2025የሀገር ውስጥ ዜና ቅዱስነታቸው ፥ ” በአደጋው በሞተ ሥጋ ለተለዩን ወገኖቻችን ዕረፍተ ነፍስን በአደጋው የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው ሁሉ ምሕረትን በመለመን ለተጎጂ ቤተሰቦችና ለመላው ምዕመናን መጽናናትን ይስጥልን ” በማለት አባታዊ የኃዘን መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። መስከረም 22/2018 ዓ.ም