አርቲስት ፍሬህይወት ባህሩ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች

አርቲስትና ኮሜዲያን ፍሬሕይወት ባህሩ ባጋጠማት ድንገተኛ ህመም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች፡፡

‎አርቲስቷ የቀለጠው መንደር፣ ፎርፌ፣ ረመጥ፣ ነቃሽ እና ሌሎች በርካታ በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት በተሰሩ ቴአትሮች ላይ ተውናለች ።
‎
‎አርቲስት ፍሬህይወት በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት በውዝዋዜ እና ዳንስ ተቀጥረው ችሎታቸውን በመድረክ ካሳዩት ከያኒያን መካከል አንዷ ነበረች።
‎
በሀገር ፍቅር ቴአትር ለበርካታ ዓመታት በሙያዋ ያገለገለችው አርቲስቷ፤ በበርካታ ፊልሞች፣ የቴሌቪዥን ድራማ እና የሙዚቃ ክሊፖች ላይ በትወና መሳተፏን የሀገር ፍቅር ቴአትር መረጃ አመልክቷል።

መስከረም 22/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *