ሳይንቲስቶቹ ሱሱሙ ኪታጋዋ፣ ሪቻርድ ሮብሰን እና ኦማር ኤም. ያጊ ናቸዉ፡፡
የኖቤል የኬሚስትሪ ሽልማት ያሸነፉት አዲስ ሞለኪውላዊ አርክቴክቸር በማዘጋጀታቸው ነዉ፡፡
ይህም ለአየር ንብረት ለውጥ እና የንፁህ ውሃ አቅርቦት እጥረትን ለመቅረፍ የሚያግዙ ቁሳቁሶችን በመስራታቸዉ ነዉ፡፡
ሦስቱ ተሸላሚዎች የሰሯቸዉ ሜታል-ኦርጋኒክ ፍሬምወርኮች ፤ ጋዞች እና ሌሎች ኬሚካሎች ሊፈስሱባቸው የሚችሉ ትላልቅ ክፍተቶች ያሏቸው እና ከበረሃ አየር ውሃ ለማምረት፣ ካርቦን ዳይኦክሳይድን ለመያዝ ወይም መርዛማ ጋዞችን ለማከማቸት ሊያገለግሉ ይችላሉ ተብሏል።
አካዳሚው እንዳለው ከእነዚህ ቁሳቁሶች ውስጥ አንዳንዶቹ በሚያስደንቅ ሁኔታ ትልቅ የገጽታ ስፋት ያላቸዉ ናቸዉ፡፡
ትንሽ የስኳር ኪዩብ የሚያክል ባለ ቀዳዳ ቁሳቁስ እንደ ትልቅ የእግር ኳስ ሜዳ የሚያክል የገጽታ ስፋት ሊይዝ ይችላል።
በዚህም ምክንያት በትናንሽ መጠን እጅግ በጣም ብዙ ጋዝ ማከማቸት ይችላል ሲሉ የኖቤል የኬሚስትሪ ኮሚቴ አባል የሆኑት ኦሎፍ ራምስትሮም ተናግረዋል።
ኪታጋዋ በጃፓን የኪዮቶ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር ሲሆኑ፤ ሮብሰን በአውስትራሊያ በሜልቦርን ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር ናቸው፡፡ ያጊ ደግሞ በዩናይትድ ስቴትስ በካሊፎርኒያ በርክሌይ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር ናቸው።
ከአንድ ምዕተ ዓመት በላይ ያስቆጠረው የኖቤል ሽልማት፤በሮያል ስዊድን የሳይንስ አካዳሚ የሚሰጥ ሲሆን፤ አሸናፊዎቹ 1.2 ሚሊየን ዶላር፤ እንዲሁም በዓለም ላይ እጅግ የተከበረውን የሳይንስ ሽልማት የማሸነፍ ዝናን ይጋራሉ ሲል የዘገበዉ ሮይተርስ ነዉ።
እስከዳር ግርማ
መስከረም 28/2018 ዓ.ም
