ዓለም እቀፍ የውሃ አስተዳደር ተቋም (IWMI) እና ዲጂታል አፍሪካ (DEAfrica) በሄልምስሌይ የበጎ አድራጎት ድርጅት (The Helmsley Charitable Trust) ድጋፍ በጋራ ያዘጋጁት ይሀ ሲምፖዚየም ውሃን በይበልጥ ውጤታማና ፍትሐዊ በሆነ መንገድ ለማስተዳደር የሚያግዝ መረጃ ለማመንጨት አዳዲስ መንገዶችን ለማቅረብ የሚያስችል እንደሆነም ተገልጿል።
በመድረኩም በከፍተኛ ጀረጃ የቴክኖሎጂ ማሳያዎችን ይታይበታል የተባለ ሲሆን፤ ከቡርኪና ፋሶ፣ ኢትዮጵያ፣ ጋና፣ ኬንያ፣ ዛምቢያ እና ሌሎች አገሮቾ የውሃ አስተዳደር መፍትሄዎችም ይቀርባሉ ተብሏል።
የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ተቋም ዋና ዳይሬክተር አብዲሳ ይልማ “ኢትዮጵያ በርካታ የውሃ አካላት አሏት በከፍተኛ የሀዝብ ቁጥር መጨመር እና እያደገ በመጣው የኢኮኖሚ ልማት ፍላጎት ሳቢያ በሁሉም ዘርፎች የውሃ ፍላጎት እየጨመረ ነው ብለዋል”፡፡
በዚህም የውሃ ሀብቶችን መረዳት፣ መጠበቅ እና ማልማት እንዲሁም ለእንደዚህ አይነቶቹ ዓላማዎች ተገቢውን መረጃ በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ ደረጃ ተደራሽ ማድረግ አስፈላጊ ነው” ብለዋል።
መድረኩ ለሶስት ቀናት እንደሚቆይም ጣቢያችን ለመረዳት ችሏል።
ለዓለም አሰፋ
ጥቅምት 11/2018 ዓ.ም
