ሐማስ ትጥቅ ለመፍታት የማይተባበር ከሆነ “ድምጥማጡ ይጠፋል” የአሜሪካው ምክትል ፕሬዚዳንት

የአሜሪካው ምክትል ፕሬዚዳንት ጄዲ ቫንስ ሐማስ ትጥቅ ለመፍታት የማይተባበር ከሆነ “ድምጥማጡ ይጠፋል” ሲሉ ተናገሩ።

ጄዲ ቫንስ የጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት አተገባባር “ከሚጠበቀው በላይ በተሻለ ሁኔታ” እየሄደ ነው፤ እንዲሁም ስምምነቱ ጸንቶ ይቆያል ብለዋል።

ቫንስ እስራኤልን በጎበኙበት ወቅት ታጣቂ ቡድኑ አሜሪካ በምክረ ሃሳቧ ላይ ያቀረበችውን እና ገና ስምምነት ላይ ያልተደረሰበትን ትጥቅ መፍታት በመጥቀስ “ሐማስ የማይተባበር ከሆነ ድምጥማጡ ይጠፋል” ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው በመካከለኛው ምሥራቅ የሚገኙ የአሜሪካ ታላላቅ አጋሮች ሐማስ ተገቢ ባልሆነ መልኩ የሚቀጥል ከሆነ “ሐማስን ለማስተካከል፣ ወደ ጋዛ በከፍተኛ ኃይል ለመግባት” ዝግጁ ናቸው ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

ቫንስ ወደ እስራኤል ያቀኑት እሁድ ዕለት በሐማስ እና በእስራኤል ጦር መካከል ግጭት ተቀስቅሶ 12 ቀናት ያስቆጠረውን የተኩስ አቁም አደጋ ላይ የወደቀ በመሰለበት ወቅት ነው።

ጥቅምት 12/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *