በጃማይካ የሚገኙ ሰዎች በሰዓታት ውስጥ በካሪቢያን ውድመት እና ከባድ ጎርፍ ያመጣል ተብሎ የሚጠበቀው የሜሊሳ አውሎ ንፋስ ተጽዕኖ በዝግጅት ላይ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
የአሜሪካ ብሄራዊ አውሎ ንፋስ ማዕከል እንደገለጸው ፤ ሜሊሳ ሰኞ ማለዳ ላይ ጥንካሬው ከፍ እያለ መጥቷል፡፡
ባለሥልጣናቱ ቀደም ሲል በሂስፓኒዮላ ደሴት ላይ የአራት ሰዎችን ሕይወት ቀጥፏል የተባለዉ ይህ አዉሎንፋስ፤ አሁንም በጥንካሬዉ እጅግ ጠንካራዉ ሊሆን ይችላል ብለዋል፡፡
የጃማይካ መንግስት ነዋሪዎች የዋና ከተማዋን ኪንግስተንን አንዳንድ ክፍሎች ለቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ የሰጠ ሲሆን፤መላው ደሴቲቱም አደጋ ላይ ናት ተብሏል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
ሐመረ ፍሬዉ
ጥቅምት 17/2018 ዓ.ም
