በሱዳኗ ኤል-ፋሸር ጦርነት ተጠናክሮ ሲቀጥል፤ ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ በበኩሉ ከተማዋን መቆጣጠሩን አሳዉቋል፡፡

የአለም መንግስታት ተወካዮች ተልዕኮ እንደገለፀው፤ በኤል-ፋሸር ከተማ ያለው ሁኔታ ተባብሷል፡፡

አርኤስኤፍ ላለፉት 18 ወራት ኤል-ፋሸርን ከብቦ የሠራዊቱ ካምፖች እና ሰላማዊ ዜጎች ላይ በተደጋጋሚ ድብደባ ሲፈጽም ነበር።

በግጭቱ ወደ 3መቶ ሺህ የሚገመቱ ሰዎች መንቀሳቀስ አለመቻላቸው ተገልጿል።

በነሐሴ ወር የሳተላይት ምስሎች በከተማዋ ዙሪያ የሰዎችን እንቅስቃሴ ለመገደብ ሰፋፊ ግንቦች መገንባታቸውን አሳይቷል።

በከተማዋ ጦርነት እየጨመረ ነው የተባለ ሲሆን፤ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ የኤል-ፋሸር ምዕራባዊ ከተማን መቆጣጠሩን አሳዉቋል፡፡

አንድ የፈጥኖ ደራሹ ኃይል ተወካይ የአዲስ መንግስት ስርዓት የሱዳን ህዝብ በነፃነት፣ በሰላምና በፍትህ መብቱን መጠየቅ እንዲችል የሚያደርግ መሰረት ነዉ ብለዋል፡፡

በ2023 የተጀመረው ይህ ግጭት ከ1መቶ ሺህ በላይ ሰዎችን ገድሏል፣ 12 ሚሊየን ሰዎችን ከቀያቸው አፈናቅሏል፤ 30 ሚሊየን ሰዎችን ደግሞ አስቸኳይ ድጋፍ እና እገዛ ፈላጊ አድርጓቸዋል፡፡

ይህም በአለም ላይ ትልቁ ሰብዓዊ ቀውስ አድርጎታል።

አር ኤስ ኤፍ ኤል-ፋሸርን ሙሉ በሙሉ የሚቆጣጠር ከሆነ ደግሞ፤ የሱዳን ጦር በዳርፉር ክልል በእጁ ስር ያለ የመጨረሻው አካባቢ በመሆኑ ትልቅ ኪሳራ ይገጥመዋል።

ሱፊያን አህመድ

ጥቅምት 18/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *