በኬንያ የባህር ዳርቻ አቅራቢያ በሚገኘው ክዋሌ 12 ሰዎችን አሳፍሮ ይጓዝ የነበረ አውሮፕላን ተከስክሶ መጥፋቱን የሀገሪቱ የአቪዬሽን ባለስልጣን አስታዉቋል።
የኬንያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን በሰጠው መግለጫ፤ አውሮፕላኑ ከባህር ዳርቻዋ ዲያኒ ወደ ኪችዋ ቴምቦ የመዝናኛ መናፈሻ ስፍራ በመጓዝ ላይ ነበር፡፡
ነገር ግን አውሮፕላኑ ከማረፉ በፊት አደጋዉ ደርሷል፡፡
አንድ የዜና ጣቢያ ፖሊስን በመጥቀስ እንደዘግበው፤ አውሮፕላኑ ውስጥ ቱሪስቶችም ተሳፍረው ነበር፡፡
የኬንያ መገናኛ ብዙሃን፤ አውሮፕላኑ በእሳት ነበልባል ውስጥ ሆኖ በአደጋው ቦታ ላይ የተበተኑትን ፍርስራሾች የሚያሳይ ምስል አሰራጭተዋል፡፡
የአደጋውን መንስኤ ለማወቅ እና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመገምገም የመንግስት ኤጀንሲዎች በቦታው ላይ እንዳሉ የአቪዬሽን ባለስልጣኑ አስታዉቋል፡፡
ሀና ሰይፉ
ጥቅምት 18/2018 ዓ.ም
