የቻይናና የአሜሪካ መሪዎች በማዕድናት እና በታሪፎች ላይ ያደረጉትን ውይይት በስምምነት አጠናቀዋል ተባለ

ዶናልድ ትራምፕ ውይይቱን አስደናቂ ማለታቸዉ ተሰምቷል፡፡

የአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይናዉ አቻቸዉ ሺ ጂንፒንግ ጋር ያደረጉትን ስብሰባ ፤አስደናቂ ብለው ሲገልጹ፤ ሁለቱ መሪዎች በደቡብ ኮሪያ ባካሄዱት ውይይት በተግባር በሁሉም ጉዳዮች ላይ መስማማታቸው ተገልጿል።

ትራምፕ ቻይና የፌንታኒል ንጥረ ነገሮችን ፍሰት ለማገድ ተጨማሪ እርምጃ እንድትወስድ፤ የአሜሪካ በበኩሏ የቻይና ሶያ አተሮችን መግዛቷን እና የማዕድናት ምርትን እንድትቀጥል ከስምምነት ደርሰዋል ተብሏል፡፡

በቻይና ሸቀጦች ላይ የጣሉትን ታሪፍም ከ57 በመቶ ወደ 47 በመቶ እንደሚቀንሱ ተናግረዋል።

ትራምፕ ከግንቦት በኋላ ቻይናን እንደሚጎበኙ እና ሺ ጂንፒንግም በተመሳሳይ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ወደ አሜሪካ እንደሚጓዙ ገልጸዋል፡፡

በስብሰባው ውጤት ላይ ቻይና እስካሁን አስተያየት አልሰጠችም ሲል የዘገበዉ ሮይተርስ ነዉ፡፡

ሱፊያን አህመድ

ጥቅምት 20/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *