ትራምፕ አገራቸዉ ከቬንዙዌላ ጋር ጦርነት ውስጥ መግባቷ ላይ እርግጠኛ አለመሆናቸዉን ተናገሩ

ጦርነት መነሳቱን እጠራጠራለሁ፤ የሚነሳ አይመስለኝም ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ የቬንዙዌላዉን አቻቸዉን ግን ከማስፈራራት ወደኋላ አላሉም፡፡

የቬንዝዌላው ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮ በሥልጣን የሚቆዩት ‹‹ለአጭር ጊዜ›› ነዉ ብለዋል፡፡

ከሲቢኤስ ጋር በነበራቸዉ ቃለ መጠይቅ ፕሬዝዳንቱ፤ የኒኮላስ ማዱሮ ቀናት አጭር ናቸዉ ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡

ይህ አስተያየት የመጣዉ፤ አሜሪካ በካሪቢያን አቅራቢያ አደንዛዥ ዕፅ ያዘዋውራሉ ያለቻቸው ጀልባዎች ላይ ጥቃት መፈጸሟን በቀጠለችበት ወቅት ነዉ፡፡

ወደ አሜሪካ የሚገባው አደንዛዥ ዕፅ እንዲገደብ እርምጃ መውሰድ ግዴታቸው መሆኑን ትራምፕ ይገልጻሉ፡፡

በርካቶች ደግሞ አሜሪካ ጥቃት እየፈጸመች ያለቸው የአደንዛዥ ዕፅ ዝውውርን ለመግታት ሳይሆን የማዱሮን መንግሥት ለማውረድ ነው በሚል እየተቹ ይገኛል።

ትራምፕ እነዚህን ትችቶች ዉቅድ አድርገዋል፡፡እርምጃዉ የሚወሰደዉ በብዙ ምክንያቶች ነው ሲሉም ተደምጠዋል።

በዚህ ሁሉ መሐል ዩናይትድ ስቴትስ ከቬንዙዌላ ጋር ልትዋጋ እንደሆነ የተጠየቁት ትራምፕ ‹‹እጠራጠራለሁ፣ አይመስለኝም›› ሲሉ መልሰዋል።

አሜሪካ ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮን በቁጥጥር ሥር ማዋል የሚያስችል መረጃ ለሚያደርሱ ሰዎች የምትሰጠውን ጉርሻ በእጥፍ አሳድጋ 50 ሚሊዮን ዶላር ማድረሷ አይዘነጋም።

ሀና ሰይፉ

ጥቅምት 24/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *