በኢትዮጲያ ውስጥ ካለው የእርሻ መሬት 43 በመቶ የሚሆነው በአሲዳማነት የተጠቃ መሆኑን በኢትዮጲያ ግብርና ኢንስቲትዩት ከፍተኛ ተመራማሪ አቶ ግርማ ማሞ አስታዉቀዋል፡፡
በኢትዮጲያ ግብርና ውስጥ በአፈር ምርታማነት ዙሪያ ዋነኛ ችግር ያሏቸውን ጉዳዮች የዘረዘሩት ተመራማሪው፤ የማዳበሪያ እጥረት፣ የአፈር አሲዳማነት እና የአፈር እርጥበት ማነስ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ተመራማሪው ይሄን ያሉት በኢትዮጵያ፣ ኬንያና ሩዋንዳ ሲሰራበት የቆየው የአየር ንብረት ተስማሚ ግብርናን ለመደገፍ የመሬት፣ የአፈርና የሰብል መረጃዎችን መለዋወጥ የሚያስችል ፕሮጀክት መጠናቀቁ በተገለፀበት ወቅት ነው፡፡
በምርታማነት ላይ እንደ ችግር የተነሱትን በመለየት ፕሮጀክቱ የመፍትሄ ስራዎችን አከናውኗል ብለዋል ተመራማሪዉ፡፡
ሌላው ተመራማሪው ያነሱት የአፈር ማዳበሪያን ጉዳይ ሲሆን፤ በተጠናው ጥናት መሰረት የኢትዮጲያ ግብርና በአብዛኛው የናይትሮጂን እና የፎስፎረስ ማዳበሪያ በቂ እንደሆነ ታምኖበት ወደ አርሶ አደሩ እየደረሰ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ፕሮጀክቱ አሁን ላይ በአማራ ክልል ባሶና ወረዳና በኦሮሚያ ክልል አዳሚ ቱሉ ተግባራዊ እየተደረገ እንደሚገኝ ተመራማሪዉ ተናግረዋል፡፡
አቤል እስጢፋኖስ
ጥቅምት 24/2018 ዓ.ም
