ሳሚያ ሱሉሁ ሐሰን ታንዛኒያን ለመምራት ለሁለተኛ ዙር ፕሬዝዳንትነት ቃለ-መሃላ ፈፀሙ

እንደ አገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን 98 በመቶ ድምጽ በማግኘት ያሸነፉት የ65 ዓመቷ መሪ፤ በኢማኑኤል ንቺምቢ ምክትል ፕሬዝዳትነት ይደገፋሉ።

ይህም እ.ኤ.አ. በ2021 የቀድሞ መሪ ጆን ማጉፉሊን ሞት ተከትሎ ሥልጣኑን ከተረከቡ በኋላ፤ ለመጀመሪያ ጊዜ በምርጫ ያሸነፉ ፕሬዝዳንት መሆናቸውን ያሳያል።

ሳሚያ በታንዛኒያ ታሪክ ውስጥ ልዩ ቦታ አላቸው። አንድም የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዝዳንት በመሆን።

ሁለትም በዛንዚባር የተወለዱ የመጀመሪያዋ ፕሬዝዳንትም ናቸው፡፡

የፖለቲካ ሕይወታቸውን የጀመሩት የዛንዚባር የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል በመሆን እና ሚኒስትር ሆነው በመሾም ነው፡፡

እ.ኤ.አ. በ2010 የታንዛኒያ ብሔራዊ ምክር ቤት አባል ሆነው የተመረጡ እና የሕብረት ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው አገልግለዋል።

እንዲሁም እ.ኤ.አ. በ2014 የሕገ-መንግስት ጉባኤ ምክትል ሊቀመንበር ነበሩ።

እ.ኤ.አ. በ2015 ደግሞ ለሟቹ ፕሬዝዳንት ማጉፋሊ የምርጫ አጋር ሆነው በመመረጥ እና ምክትል ፕሬዝዳንትነቱን ቦታ በመያዝ የመጀመሪያዋ ሴት ሆነዋል እንደ ስፑትኒክ ዘገባ፡፡

ጥቅምት 25/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *