በየዓመቱከሚወለዱ 10ሺህ ህፃናት በ83ቱ ላይ የነርቭ ዘንግ የአፈጣጠር ችግሮች ይከሰታሉ።
ይህ ቁጥር ከምዕራባውያን አገራት ጋር ሲነፃፀር የ8 በመቶ ብልጫ አለው።
ይህ ችግር ከሚከሰትባቸው አገራት መካከል በአፍሪካ አንደኛ በአለም ደግሞ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠናል።
የነርቭ ዘንግ አፈጣጠር ችግር በተለይም የነርቭ ዘንግ ክፍተት እና የጭንቅላት ውስጥ ፈሳሽ ከመጠን በላይ ክምችት በአገራችን በየአመቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ህፃናት ላይ የሚከሰት የአፈጣጠር ችግር ነው።
ለዚህ የጤና ችግር መፈጠር እንደ ምክንያት የሚጠቀሰው ዋነኛው ጉዳይ የፎሊክ አሲድ ዕጥረት ነው።
አዲስ ከሚወለዱ 10 ሺህ ህፃናት 8.8 በመቶዎቹ ከነርቭ ዘንግ ክፍተት ችግሮች መሀል አንዱ የሆነው የጭንቅላት ውስጥ ፈሳሽ ከመጠን በላይ ክምችት ይከሰትባቸዋል።
ከባድ የሆነ የነርቭ ዘንግ ክፍተት ካለባቸው ልጆች መካከል 80 በመቶ የሚሆኑት ላይ የጭንቅላት ውስጥ ፈሳሽ ከመጠን በላይ ክምችት የነርቭ ዘንግ አፈጣጠር ችግር ይኖርባቸዋል።
ቀድሞ የተወለዱ ልጆች ላይ ይህ ችግር ካለ ቀጣይ የሚወለዱ ልጆች ላይ የመከሰት ዕድል አለው የተባለ ሲሆን፤ከእርግዝና በፊት የነበሩ ኢንፌክሽኖች፣ የሚጥል ህመም ያለባቸው እና መድኃኒት የሚወስዱ እናቶች፣ የስኳር ታማሚ እናቶች ለዚህ ችግር የተጋለጡ ልጆችን ሊወልዱ ይችላሉ።
ዕድሜያቸው ለማርገዝ የደረሱ ሴቶች በተለይ ከ18 ዓመት ጀምሮ የፎሊክ አሲድ እንክብልን መውሰድ እና የቅድመ እርግዝና ክትትል ማድረግ ችግሩን አስቀድሞ ለመከላከል የሚረዱ መንገዶች ናቸው።
ከዚህ ችግር ጋር የተወለዱ ህፃናት ከ24 እስከ 48 ሰዓት ውስጥ መምጣት ቢችሉ ችግሩ መስተካከል የሚችል መሆኑ ተገልጿል።
ሆፕ ኤስ ቢ ኤች ከጤና ሚኒስቴር እና ከሌሎች ተቋማት ጋር በመተባበር አለምአቀፍ የነርቭ ዘንግ ክፍተት እና የጭንቅላት ውስጥ ፈሳሽ ከመጠን በላይ ክምችት የነርቭ ዘንግ የአፈጣጠር ችግሮች ቀንን እያከበረ ነው።
እስከዳር ግርማ
ጥቅምት 27/2018 ዓ.ም
