አዲስ ጥናት እንደሚያመለክተው የደም ስኳርን ለመቆጣጠር እና የስኳር በሽታን ለመከላከል ክብደት ማንሳት ትሬድሚል (የመሮጫ ማሽን )ላይ ከመሮጥ የበለጠ ውጤታማ ነው፡፡
ከቨርጂኒያ ቴክ ፍራሊን ባዮሜዲካል ምርምር ተቋም የመጣ ቡድን ክብደት ማንሳት ሰውነት ስኳርን እና ስብን የሚያስተዳድርበትን መንገድ በማሻሻል የተሻለ ውጤት ሊያስገኝ እንደሚችል አረጋግጧል።
የተለያዩ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች በምግብ መፈጨት ላይ እንዴት ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩ ለመረዳት፣ ተመራማሪዎች አይጦችን ከፍተኛ ስብ የበዛበት ምግብ ይመግቧቸዋል፡፡
ከዛም አይጦቹን በሁለት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ቡድኖች በመክፈል ግማሾቹን በሽክርክሪት ላይ እንዲሮጡ ሲያደርጓቸው፤ ሌሎቹን ደግሞ ምግባቸውን ለማግኘት ክብደት ያለው በር ያስነሷቸው ነበር፡፡
ከበርካታ ሳምንታት በኋላም ሁለቱም ቡድኖች ከማይንቀሳቀሱ አይጦች ጋር ሲነፃፀሩ ትልቅ የጤና መሻሻሎችን አሳይተዋል፤ይህም አነስተኛ የሰውነት ስብ፣ የተሻለ የደም ስኳር ቁጥጥር እና ሰውነታቸው የተሻለ የግሉኮስ አጠቃቀምን አሳይቷል ተብሏል፡፡
ነገር ግን ክብደት እንዲያነሱ የተደረጉት አይጦች ከሁሉም የተሻሉ ሆነው ስለመገኘታቸው ጥናቱ አሳይቷል፡፡
የፍራሊን ባዮሜዲካል ምርምር ተቋም እና የቪቲሲ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ሕክምና ምርምር ማዕከል ፕሮፌሰርና ዳይሬክተር የሆኑት ዠን ያን ጥናታችን እንደሚያሳየው ሩጫም ሆነ ክብደት ማንሳት የሰውነት ስብን ለመቀንስ እና የደም ስኳር መጠንን ለመጠበቅ ይረዳል ብለዋል
ዘገባው የፎክስ ኒውስ ነው
ሐመረ ፍሬው
ጥቅምት 27/2018 ዓ.ም
