የኢትዮጵያ ህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም በ2018 አመት የሩብ አመት የስራ ግምገማ ሪፖርቱን አዉጥቷል።
የኢትዮጵያ ህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም በሩብ አመቱ ባከናወነው የምርመራ እና ክትትል ስራ 83 በመቶ የአስተዳደር በደል አቤቱታ በመንግሥት ተቋማት ላይ መቅረቡን ገልጿል።
17 በመቶ ያህሉ ደግሞ በግል ተቋማት ላይ የቀረቡ የአስተዳደር አቤቱታዎች መሆናቸዉን ሪፖርቱ ጠቁሟል።
በዚህም የአስተዳደር በደልን አቤቱታ ተንተርሶ የአስተዳደር በደል ለመከላከል ተደርጓል በተባለ ቁጥጥር መሠረት ሰባት ጉዳዮችን መሠረት በማድረግ በዘጠኝ ተቋማት ቁጥጥር ተደርጓል ተብሏል።
በዚህ የቁጥጥር ስራም በ35 ጉዳዮች ላይ ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በመወያየት ከስምምነት መደረሱን ተቋሙ አስታዉቋል፡፡
ቁጥጥር ከተደረገባቸው በሀረሪ ÷ በቤንሻንጉል ÷ በጋምቤላ÷ በደቡብ ኢትዮጵያ እና በትግራይ ክልላዊ መንግስት ከተሞች በሚገኙ መስሪያ ቤቶች ላይ ቁጥጥር መካሄዱን መግለጫዉ ይጠቁማል።
ተቋሙ በአስተዳደር በደል ምርመራ እና ማረም በሩብ አመቱ 7መቶ50 አቤቱታዎች ለመቀበል ቢያቅድም 4መቶ31 አቤቱታዎችን መቀበሉን አሳዉቋል።
በዚህም 18 ሺህ 1መቶ81 ሰዎች የአስተዳደር በደል ተፈፅሞባቸዉ አቤቱታቸዉን ለኢትዮጵያ ህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም አቅርበዋል።
አቤቱታዎቹ ዉስጥ 47 በመቶ ያህሉ በተቋሙ ስር የሚወድቁ ሆነዉ በመገኘታቸዉ የምርመራ ሂደት ላይ ይገኛሉ ተብሏል።
በሩብ አመቱ ከዚህ በተጨማሪ በአጠቃላይ 43 ያህል የአቤቱታ አይነቶች እንደቀረቡለት በላከዉ መግለጫ ላይ ተመልክተናል።
ቁምነገር አየለ
ህዳር 05/2018 ዓ.ም
