የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ እናት ፓርቲ ከቅንጅት መሰረዙን ተከትሎ ከአምስት ቀናት በፊት ላወጣዉ መግለጫ ምላሽ ሰጥቷል።
ቦርዱ በኦዲት አገኘሁት ካለው ጉዳዮች መካከል፥ፓርቲው ከአባላት ለሰበሰበው መዋጮ የገንዘብ መቀበያ ደረሰኝ ያለመስጠቱን እና በፓርቲው ስም በሦስት ባንኮች ላይ የሚገኘውን ገንዘብ ትክክለኛነት ማረጋገጥ አለመቻሉ ተገልጿል።
እናት ፓርቲ በምርጫ ቦርዱ የተገለጹትን ኦዲቱን የተመለከተ ግኝቶቹን ማጣጣሉ ይታወሳል።
ፓርቲው ከቅንጅቱ የተገለለበትን ሂደትም ለ14 ወራት ፓርቲውን ለማፍረስ ሲደረግ የከረመ ጥረት በማለት ከመጥራቱም ሌላ የኦዲቱን ግኝትም ትክክል አለመሆኑን ጠቅሶ እንደነበር የሚታወስ ነው።
በፓርቲው አንዳንድ አመራሮች ከፍተኛ የሕግና የፓርቲው የመተዳደሪያ ደንብን በመጣስ ብሔራዊ ሥራ አስፈጻሚ ሹመት መከናወኑን ገልጿል ቦርዱ።
የፓርቲው ገንዘብ ላልተባለለት አላማ የዋለ መሆኑን አንስቶ ፥ግልፅ ያልሆነ አከፋፈልና አስተዳደር በፓርቲው ፕሬዚዳንት ፍላጎት ብቻ ገንዘብ ወጭ መደረጉ በሪፓሪቱ አመላክቷል።
ምርጫ ቦርድ ፓርቲው ቀጣይ የበጀት ድጋፍ ከመንግስት ከመቀበሉ በፊት ህጉ በሚያዘው መሰረት እናት ፓርቲ በ2016 ዓ.ም ከመንግስት ያገኘውን በጀት አስመርምሮ እንዲያቀርብ መደረጉን ገልጿል።
ሊዲያ ደሳለኝ
ህዳር 16/2018 ዓ.ም
