የ2018 ዓ.ም. 9ኛ ኦዳ አዋርድ ህዳር 30 ይካሄዳል ተባለ፡፡

በኪነጥበቡ ዘርፍ ለተከታታይ ዘጠኝ ዓምታት ከ2010ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩን የኪነጥበብ ባለሞያዎችን እየሸለመ እና እያበረታታ የዘለቀው አዳ አዋርድ ዘንድሮም ለ9ኛ ጊዜ መርሃግብሩን የፊታችንሕዳር 30 ቀን 2018 ዓ.ምበአዲስ አለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ጀምሮ እንደሚከናወን ተገልጿል።

ይህ ዝግጅት ለሀገር ብሎም ለአህጉራችን አፍሪካ አበርክቶው ትልቅ መሆኑን እና ከሌሎች አፍሪካ ሃገራት ጋር ለሚኖረን የኪነጥበብ እና የባህል ልውውጥ ድርሻ እንደሚኖረው ተጠቅሷል፡፡

ኦዳ አዋርድ በዋነኝነት ከኢፌዲሪ የውጭጉዳይሚንስቴር፣ ከባህልና ስፖርት ሚንስቴር እንዲሁም ከቱሪዝም ሚንስቴር ጋር በጥምረት የሚዘጋጅ ነው ተብሏል።

ዘንድሮ ለዘጠነኛ ጊዜ በሚያዘጋጀው የሽልማት መርሃግብርም ከቀደምት ዓመታት ውድድሮች ለየት ባለ መልኩ በመቅረብ ትኩረቱን ሙሉ በሙሉ በሙዚቃው ዘርፍ ላይ ብቻ በማተኮር የሽልማት ስነስርዓቱን እንደሚያከናውን ዝግጅቱን በማስመልከት በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተነስቷል ።

በመሆኑም በሙዚቃው ዘርፍ ብቻ ከሀገር ውስጥ 30 እጩዎችን በ6 የሽልማት ዘርፎች ለምርጫ ያቀረበ ሲሆን ከሀገር ውስጥ እጩዎች በተጨማሪ ከ12 አፍሪካ ሃገራት የተወጣጡ እጩዎችን ለህዝቡ ይፋ እንደሚያደርግ ተነግሯል ።

በ AFRICAN SUPER STAR ዘርፍ ላይ ተሸላሚ ለመሆን የሚሳተፉት 12 የአፍሪካ ሃገራትም ሩዋንዳ፣ማሊ፣ሞሮኮ፣ አንጎላ፣ማዳጋስካር፣ኬንያ፣ጅቡቲ ፣ ሲሼልስ፣ጋና፣ቶጎ፣ደቡብ ሱዳን እና ኡጋንዳ ናቸው ተብሏል፡፡

የ2018 ዓ.ም እጩዎችተሽላሚ የሚሆኑት ሙሉ በሙሉ ከአድናቂዎቻቸው በሚያገኙት ድምጽ ሲሆን ድምጽ የሚሰጥበት ሂደትም ከህዳር 16/ 2018 ጀምሮ ለዚሁ ዝግጅት በሚያገለግለው የኦዳ አዋርድ ድረ ገጽ (www.oddaaward.com) መሆኑ ተገልጿል፡፡

ሐመረ ፍሬው

ህዳር 16/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *