ፕሬዝዳንት ቭላዲሚር ፑቲን በሞስኮ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ውይይት ከማድረጋቸው በፊት የዩክሬን ግዛትን በተመለከተ የያዙትን ፍላጎት እንደገና አጠናክረዋል ተባለ፡፡

ፕሬዝዳንት ቭላዲሚር ፑቲን በዩክሬን ያለውን ጦርነት ለማቆም የያዙትን ዋና ዋና ፍላጎቶች እንደገና ማጠናከራቸው ተገልጿል፡፡

ፑቲን ሩሲያ በኃይል የያዘቻቸውን የዩክሬን ግዛቶች ህጋዊ እውቅና እንዲያገኙ ከረጅም ጊዜ ጀምሮ ሲወተውቱ መቆየታቸው ተጠቅሷል፡፡

እነዚህም በ2014 የተጠቃለለችውን የደቡቧን ክሪሚያ ባሕረ ገብ መሬት እና በአብዛኛው ሞስኮ አሁን የያዘችውን የምሥራቃዊውን ዶንባስ ክልል ያካትታሉ።

በኪየቭ በኩል ግን እስካሁን ድረስ በእጇ ያሉትን የዶንባስ ክፍሎች አሳልፋ ለመስጠት ፈቃደኛ ስላለመሆኗ ተነግሯል፡፡

ከፑቲን ንግግር በኋላም ሀሳባቸውን የሰጡት የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ሩሲያ “ጦርነቱን በእውነት ለማቆም” የሚደረጉ ጥረቶችን “በንቀት አይታዋለች ሲሉ”ስለመግለፃቸው ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ሐመረ ፍሬው

ህዳር 19/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *