የምግብ ዘይትን በመከዘን ሰዉ ሰራሽ የምርት እጥረት ለመፍጠር የሞከሩ ከ20 በላይ ተሳቢ ተሽከርካሪዎች ምርቶቻቸዉን ወደ ገበያ እንዲያሰራጩ  መደረጉ ተገለፀ‌

‎‎ይህንን ያስታወቀው የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ነው።‎‎የቢሮው ሀላፊ ወይዘሮ ሀቢባ ሲራጅ እና ሌሎች የቢሮዉ ሀላፊዎች በመርካቶ ገበያ ተገኝተዉ የንግድ እንቅስቃሴ ምልከታ ማድረጋቸውን ንግድ ቢሮው አመልክቷል።

ከተደረገው‌‎ ምልከታ በኋላ ሀላፊዋ የምግብ ዘይት እጥረት ችግር እንዳለ በማህበራዊ ሚዲያ የሚናፈሰዉ ወሬ ሀሰተኛ ነዉ ብለዋል።

‌‎በተጨማሪም ምርትን በመከዘን ሰዉ ሰራሽ የምርት እጥረትን የሚፈጥሩ ነጋዴዎች ላይ ቢሮዉ ተጨባጭ እርምጃን ይወስዳል ነው ያሉት።
‎
‎በ እለቱም የምግብ ዘይትን በመከዘን ሰዉ ሰራሽ የምርት እጥረት ለመፍጠር የሞከሩ ከ20 በላይ ተሳቢዎች ምርቶቻቸዉ ወደ ገበያ እንዲሰራጭ መደረጉን ገልፀዋል።

አቤል እስጢፋኖስ

ህዳር 22/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *